ስለ እኛ

Building skills, teamwork, and community spirit through football.

ስለ የኛ አዲስ ከቴ ምስረታ

በእግር ኳስ ፣ የጋራ መንፈስ የማህበረሰብ እሴትን እንገነባለን!

የኛ አዲስ ከተማ

በቅድመ አያቶቻችን የተመሰረተችው አዲስ ከተማ የታሪክና የባህል ቅርስዋን ከትውልድ ወደ ትውልድ ሲያስተላልፍ ቆይታለች። ነገር ግን የዘመኑ ትውልድ እያጋጠመው ያለው የወጣቶች ሱሰኛነት፣ አልታዘዝ ባይነት እና አጓጉል ተግባሮች ማህበረሰቡን እጅግ አሳሳቢ ደረጃ ላይ አድርሰውታል። በሌላ በኩል ግን ብዙ ተስፋ ያላቸውና ታለንት የተሞላባቸው ታዳጊዎችና ወጣቶች መኖራቸው ።

ይህንን ሁኔታ በመገንዘብ እና ከቅርብ ጓደኞቹ ጋር በመማካር ወጣቶችን በስነምግባር ማነጽና በስፖርት መንገድ አቅማቸውን ማሳደግ ለአዲስ ከተማ፤ለአካባቢው እና ለአገር ከፍተኛ አስተዋጾ እንደሚያበረክት በአባይ ምንጭ ቡና እየጠጡ ባደረጉት ውይይት ተስማሙ። በዚሁ መሠረት በ2011 ዓ.ም. በወቅቱ ተጫዋች እና አሁን አሰልጣኝ በሆነው ኢብራሂም ረሺድ መሪነት ክለቡ ተመሰረተ።

ክለቡ ዋና ዓላማው ወጣቶችን ከአደገኛ ተግባሮች ማራቅ፣ በስፖርት ብቃት በስነምግባር ማበረታታት ፡ ለከተማው እና ለአገሩ ጠቃሚ ዜጎች ማድረግ ነው። ከተመሰረተ ጀምሮ ክለቡ በማህበረሰቡ ውስጥ አስፈላጊ ሚና በመጫወት ብዙ ወጣቶችን ወደ ተሻለ የሕይወት መንገድ እየመራ ይገኛል።

የክለባችን የውድድር ጨዋታዎች ተጫዋቾቻችንን እና ደጋፊዎቻችንን አንድ ላይ የሚያቀራርቡ ናቸው ። እያንዳንዱ ጨዋታዎቻችን የእግር ኳስ፣ የቡድን ስራ እና የማህበረሰባችን ድጋፍ ውጤቶች ናቸው። ተጫዋቾች ችሎታቸውን ያለ ስስት ያሳያሉ፣ የከቴ ደጋፊዎችም ስታዲየሙን በኃይልና በእንቅስቃሴ ይሞላሉ፤ ለእያንዳንዱ ጎል ፤ ደስታ ጩኸት እና ለ ድክመታችን ደግሞ አበረታች ድጋፍን ያለስስት ይለግሱናል፡፡ ምንግዜም " አንድ ክለብ አንድ ቤተሰብ " በሚል መፈክር ይበልጥ ጎላ ብለን ደምቀን እንታይለን።

ለደስታውም ፣ ለፍቅሩ እና በሜዳ ላይ ለማይረሱ አስደናቂ ቅጽበቶች የኛ አዲስ ከቴን ይቀላቀሉ!

"The roar of the crowd is the fuel; the game is the fire."

ለቡድናችን ፍቅርና ድጋፍ ለማሳየት ይፋዊ የክለባችን መለያዎችን! ይግዙና በኩራት ይልበሱት!

የየኛ አዲስ ከቴ እግር ኳስ ክለብን የተለያዩ ማልያዎችን፣ የክለቡ አርማ ያረፈባቸው ቲሸርቶች፣ እንዲሁም የተለያዩ ቁሶችን በመግዛት ይደግፉን! የማልያ ሱቃችን ከፍተኛ ጥራት ያላቸው የውድድር ኪቶች፣ የስልጠና ልብሶች እና የደጋፊዎች አልባሳት በክለቡ ቀለሞች ማለትም ቀይ፣ ጥቁር፣ ነጭ፣ ሰማያዊ እና ቢጫ ቀለማት ያቀርባል። ታማኝ ደጋፊ ቢሆኑ ወይም ስጦታ ለወዳጆ ለመስጠት ቢፈልጉ በተመጣጣኝ ዋጋ ከእኛ ጋር ያገኛሉ ፡፡ ማሊያዎቻችን ምቾት እና ጥንካሬን ባካተተ ሁኔታ የተሰሩ ናቸው።

የሚወዷቸውን ተጫዋቾች የሚለብሱትን ቀለም በመልበስ ለክለቡ ያለዎትን ፍቅር ይግለጹ።

ከዋና (Home) እና ከውጭ (Away) ኪቶች ጀምሮ እስከ ልዩ እትም የደጋፊዎች ልብስ ድረስ፣ እያንዳንዱ እቃ በውድድር ቀን ወደ ጨዋታው እንዲቀርቡ በጥንቃቄ አሰርተን እናቀርባለን ። ቡድኑን ይደግፉ፣ ክለቡን ይወክሉ፣ እና ኩራታችሁን ከየኛ አዲስ ከቴ ጋር ይልበሱ!

Celebrate your passion for the club by wearing the same colors as your favorite players. From home and away kits to limited edition fan apparel, every item is crafted to bring you closer to the action on match day. Support the team, represent the club, and wear your pride with Yegna Addis Kete FC!

የክለባችንን መለያዎች ከእኛ ይግዙ

የውድድር ጨዋታዎች ጊዜ / matchday vibes

ደጋፊዎቻችን

ደጋፊዎቻችን የክለባችን መሠረት ናቸው። እነሱ የሜዳው ኃይል፣ የቡድኑ መንፈስ እና የድል ተስፋ ናቸው። ከመጀመሪያዋ ጩኸት እስከ መጨረሻው ጊዜ ድረስ በጽናት ይቆማሉ፤ ቡድናችንን በሙሉ ልብ ይደግፋሉ።

በድል ጊዜ በደስታ ይዘምራሉ፣ በሽንፈት ጊዜ ያበረቱናል። ድምፃቸው ሜዳውን ያንቀጥቃል፤ መንፈሳቸው ተጫዋቾቻችንን ያበረታታል። በአንድነት ይንቀሳቀሳሉ፣ በክብር ይደግፋሉ፣ ሁልጊዜም የአዲስ ከቴን ስም ከፍ እያደረጉ ይዘምራሉ።

ደጋፊዎቻችን በሜዳ ውስጥ ብቻ አይታዩም፤ክለባችን በማህበራዊ እንቅስቃሴዎች፣ በበጎ አድራጎት እና በማኅበረሰብ ልማት ውስጥ ድጋፍ ሲጠይቅ እጅ ይዘርጋሉ ያግዛሉ። ክለባችን ከማኅበረሰቡ ጋር እንዲቀራረብ ታላቅ ሚናም ይጫወታሉ።

አንድ ክለብ አንድ ቤተሰብ!