ሁሌም በስኬት እንጓዛለን

At Yegna Addis Kete, we believe in growing together through football, fostering talent and community spirit in Addis Ababa.

የደስታችን ተካፋይ ይሁኑ

Captured glimpses that tell stories beyond words.

በአሚን አጠቃላይ ሆስፒታል እና በክለባችን መካከል የስፖንሰር ሺፕ ትብብርን አስመልክቶ የትደረገ የፊርማ ስምምነት መርሃግብር

ሳሚ ካሳ ፡ ታደለ ሮባ፡ የ አብዱኪያር ተወካይ ወንዴ እንዲሁም ካሙዙ ካሳ ክለባችንን ስለጎበኛችሁ እና በነበረን ወይይት ስላሳያችሁን ድጋፍ ከልብ እናመሰግናለን ፡፡

ስላደረጋችሁት ሁሉ እናመሰግናለን በቀጣይ በብዙ መልኩ የናንተን ድጋፍ እና አብሮነት ያሻናል በመሆኑ ያደግንባትን መርካቶ እና አካባቢዋን በበጎ ለማስጠራት የጀመርነውን ዉጥን ከዳር ለማድረስ የናንተ ድጋፍ እና ትብብር በብዙ መልኩ አንፈልጋለን ፡፡ ደግሞም ስለጉብኝታችሁ ከልብ እናመሰግናለን

ሳሚ ካሳ (ሳንፎድ) ዘ አዲስ ከተማ ፡ታደለ ሮባ ፡ ካሙዙ ካሳ ፡ የ አብዱ ኪያር ተወካይ (ወንዴ) እና በወቅቱ ለነበራችሁ በሙሉ በክለባችን ስም ምስጋናችን ይድረስ

የአዲስ ከተማው ተወላጅ ወደ ትውልድ ሰፈሩ ተመልሶሀል

ከ14 አመት የስደት ቆይታ በዋላ ወደ ትውልድ ሀገሩ ሲመለስ ወደ ትውልድ እና እድገቱ ሰፈር መርካቶ በመምጣት ሰፈሩን በጎበኘበት ወቅት

ከየኛ አዲስ ከቴ የእግር ኳስ ክለብ አመራሮች እና የቦርድ አባላት ጋር ሰፊ እና ጥሩ የሚባል ስብሰባ አድርጎሀል፣ በዚህም መሰረት ለአርቲስት ሳሚ ካሳ (ሳንፎድ)

ከክለቡ አመራሮች ሰፋ ያለ ማብራሪያ የቀረበለት ሲሆን ከቀረበለት ማብራሪያም በዋላ አርቲስቱ በብዙ መንገድ ከክለቡ ጎን እንደሚቆም እና በዙሪያው ካሉ የሙያ አጋሮቹ በተለይ ደግሞ የአካባቢው ተወላጅ ከሆኑቱ አርትስቶች ጋር በመሆን ከክለቡ ጎን ቆመው ሰፋ ያሉ ስራዎችን እንደሚሰሩ ቃል ገብቶልናል ሳሚ ካሳ (ሳንፎድ) ለሰፈሩ ያለውን ትልቅ ፍቅር እና አክብሮት በተለያየ ጊዜ ባገኘው አጋጣሚ እና ኢንተርቪው መሀል የሰፈሩን ስም በኩራት ከሚያነሱ የአካባቢያችን ተወላጆች መሀል እና ግንባር ቀደም ከሆኑት ውስጥ የሚመደብ ሲሆን በዚህም መሰረት ከረጅም ጊዜ በዋላ ወደ ትውልድ ሀገሩ እና ሰፈሩ ሲመለስ የአብራኩን ክፋይ አብሮ በማምጣት ስለ ወጣበት ማህበረሰብ ያለውን ክብር በተግባር አሳይቶናል ፡፡

ሳሚ ካሳ (ሳንፎድ ) እንኳን ለሀገርህ መሬት አበቃህ🙌

እንኳን በደህና መጣችሁ!

Capturing the beauty in everyday scenes and special memories.

ደማቅ ኩነቶች

Snapshots capturing our passion and unity on and off the field

የወጣቶች ስልጠና

Building skills and community through football.

ክለባችን ውስጥ ካሉ ዘርፎች ዉስጥ አንዱ የወጣቶች ስልጠናችን ነው ታዳጊ ወጣት ተጫዋቾች በእግር ኳስ ዓለም ውስጥ ብርቱ መሠረት እንዲገነቡ የተቀናጀ ፕሮግራም ቀርጸን እየተገበርን ነው። በዚህ ፕሮግራም ውስጥ ታዳጊ ልጆች በህብረት፣ሆነው የተግባር ልምምድ ያደርጋሉ።

🔹 1. የፕሮግራሙ አላማ

  • ታዳጊ ወጣቶች በእግር ኳስ መሠረታዊ ችሎታዎች እንዲማሩ

  • በአካል ብቃት እና በታክቲክ ግንዛቤ እንዲያድጉ

  • በቡድን መስራት፣ ዲሲፕሊን እና በራስ መተማመን እንዲያጠናክሩ

  • ስፖርቱን በደስታ እንዲወዱ እና በቀጣይ የላቀ ደረጃ እንዲደርሱ

🔹 2. የስልጠና ዘዴ

የስልጠናችን ሶስት ዋና ጉዳዮች ፦

✔ ቴክኒክ ልምምድ

  • ኳስ መቆጣጠር

  • ኳስ በትክክል ማስተላለፍ

  • ፍጥነት ያለው አስተላለፍ

✔ አካል ብቃት

  • ፍጥነት እና ቅልጥፍና

  • ብርታት እና ትኩረት

  • ብቁ የአካል እንቅስቃሴ

✔ ታክቲክ እውቀት

  • ቦታ መያዝ

  • የቡድን እንቅስቃሴ

  • የጨዋታ አስተዳደር

🔹 3. የሰልጣኞች ተሞክሮ

ታዳጊዎች በአካል ብቃት በመንፈስ ጥንካሬ እና በ ዲሲፕሊን አየተኮተኮቱ እንዲበቁ ይደረጋል። እያንዳንዱ ልጅ ችሎታው ይገመገማል፣ እንዲሁም በቡድን ውስጥ ያለው ተግባቦት ይታያል ከ ስልጠና ውጭም በትምህርታቸው ጎበዝ እንዲሆኑ ክትትል እና ግምገማ እናደርጋለን ይህም ታዳጊው ትምህርቱም ላይ ትኩረት እንዲያደርግ እና ጎበዝ ተማሪ እንዲሆን ይረዳል።

በስልጠና ውስጥ የሚገኙት፦

  • ለጫወታ ህጎች መገዛት

  • የቡድን ህገ ደንብ ማክበር

  • በራስ መተማመን እና የባህሪ ግንባታ

🔹 4. የታድጊ ሰልጣኞች እድገት ግምገማ?

  • በችሎታ እድገት

  • በቡድን መስራት እና የተሻለ ተሞክሮ ማግኘት

  • በጨዋታ ውስጥ የተሻለ ውሳኔ መስጠት

  • በአእምሮ ጠንካራ መሆንን

🔹 5. ለማን ይሆናል?

ይህ ፕሮግራም ለ፦

  • ጀማሪ ተጫዋቾች

  • ችሎታቸውን ለማሻሻል የሚፈልጉ ታዳጊ ወጣቶች

  • በቡድን መስራት ልምድ ለማግኘት የሚፈልጉ ልጆች

  • በእግር ኳስ የወደፊት ተስፋ ያላቸው ታዳጊ ተጫዋቾችን

የፕላቲኒየም ስፖንሰር