

Addis Kete delivered a dominant performance, securing a convincing 3–0 victory over Denbidolo.
From the opening whistle, Addis Kete controlled the tempo of the game, showing confidence, sharp passing, and strong attacking intent.
The team created multiple chances early on and capitalized efficiently, putting pressure on Denbidolo’s defense throughout the match. Their disciplined structure and energy made it difficult for the opposition to respond.
🏆 Match Overview
Addis Kete showed strength in all areas of the pitch:
⚡ Attack: Clinical finishing with three well-taken goals
🎯 Midfield: Excellent control and ball distribution
🛡️ Defense: Solid and organized, keeping a clean sheet
🔥 Teamwork: Strong coordination and high intensity
Denbidolo struggled to break through and were unable to convert their few opportunities.
Addis Kete delivered a total domination over Denbidolo
በኢትዮጵያ ሊግ አንድ እየተሳተፈ የሚገኘው አዲስ ከቴ እግር ኳስ ክለብ ለሁለተኛው ዙር ውድድር ልምምድ እያደረገ ይገኛል።
የካቲት 10/2018 ዓ.ም
በኢትዮጵያ ሊግ አንድ እየተሳተፈ የሚገኘው የኛ አዲስ ከቴ እግር ኳስ ክለብ
በሁለተኛው ዙር ከየካቲት 14 ጀምሮ በምድብ "ለ" በሃላባ ከተማ ለሚደረገው ውድድር አስፈላጊውን ዝግጅት እያደረገ እንደሚገኝ ተገልጿል።
በኢትዮጵያ ሊግ አንድ ለመጀመሪያ ጊዜ ተሳትፎ እያደረገ የሚገኘው የኛ አዲስ ከቴ እግር ኳስ ክለብ በመጀመሪያው ዙር በምድብ 4ተኛ ደረጃ ይዞ ማጠናቀቁ ይታወሳል።
ክለቡ በሁለተኛውን ዙር ውድድር ጠንካራ ተፎካካሪ ሆኖ እንድቀርብ ለተጫዋቾች ጥሪ በማድረግ ልምምድ መጀመሩን የክለቡ ሥራአስኪያጅ አቶ አሸናፊ ሲዳ ገልጸዋል።
ክለቡ በመጀመሪያ ዙር ያጋጠሙ ተግዳሮቶች በመለየት በሁለተኛው ዙር የተሻለ ውጤት እንዲያስመዘግብ ለማስቻል ህብረተሰቡ ለክለቡ አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርጉ አቶ አሸናፊ ጥሪያቸውን አቅርበዋል። አቶ አሸናፊ አክለውም የክለቡ አባላት በቀጣይ ቀናት የምድብ "ለ" ውድድሩ ወደሚካሄድበት ሃላባ ከተማ እንደሚያቀና ተናግረዋል።
ለመጀመሪያ ጊዜ ተሳትፎ ማድረግ የቻለው አዲስ ከቴ እግር ኳስ ክለብ በመጀመሪያው ዙር ድንቅ እንቅስቃሴ ማድረጉን የገለፁት የክለቡ ቡድን መሪ አቶ ምንተስኖት አብቴ የተስተዋሉ ክፍተቶችን ለመቅረፍ አስፈላጊውን ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል።
የኢትዮጲያ ሊግ አንድ ውድድር እንደቀጠለ ነው ዛሬ የካቲት 19፣ 2018 ዓም ፡ በሃላባ ስታዲየም የኛ አዲስ ከቴ ከ ሮቤ ከተማ ባደረግነው ጨዋታ አንድ አቻ ተለያይተናል በድምቀት እየተካሄደ ባለው የኢትዮጵያ ሊግ አንድ ውድድር የኛ አዲስከቴ 62 ተኛው ደቂቃ ላይ በኢብራሂም አቡበከር አማካኝነት ባስቆጠራት 1 ጎል አቻ ሆነነ ጨዋታውን አጠናቀናል






ክለባችንን እናግዝ
በሃላባ እየተካሄደ በሚገኘው የሊግ አንድ ውድድር ይበልጥ ውጤታም ለመሆን እና ውድድሩን በስኬት ለማጠናቀቅ የደጋፊዎቻችንን ትኩረት እና ድጋፍ እንፈልጋለን በመሆኑ ክለባችንን እናግዝ የአባልነት ግዴታችንንም እንወጣ ፡፡
