Our players represent hard work, commitment, and strong spirit. We believe that success comes from teamwork, practice, and determination. Together we play, fight, and win as one family




ማህበራዊ አገልግሎት
ክለባችን በማህበረሰባችን ውስጥ በተቻለ መጠን አዎንታዊ እና ቋሚ ለውጥ ለመፍጠር ሁሌም ይተጋል ደጋፊዎቻችንን በማስተባበር በተለያዩ ችግር ውስጥ የሚገኙ አቅመ ደካሞችን በማህበራዊ ድጋፍ ዉስጥ አስገብተን ለመርዳት እና ማህበራዊ ግዴታችንን ለመወጣት እየሰራን ነው ፡፡ የኛ አዲስ ከቴ በተለያዩ ምክንያቶች የሰብአዊ ድጋፍ አገልግሎቶችን ለሚፈልጉ የማህበረሰባችን ክፍሎች ዉስጥ በመግባት በአይነት አና በገንዘብ ድጋፍ አድርገናል ወደፊትም ይቀጥላል፡፡
ክለባችን ማህበራዊ ድጋፍ ተግባራት ላይ ከሃገር ዉስጥና ከ ዉጭ ሃገራት የሚገኙ የክለባችን ደጋፊዎችን በማስተባበር ለወገኖቻችን ከትምህርት ቤት ቁሳቁስ እስከ አካል ጉዳተኛ መሽከርከሪያ (wheelchair) ድጋፍ አድርገናል።
ፕሮግራሞቻችን ዉስጥ የማህበራዊ የድጋፍ አገልግሎት በመጨመር ከ እግርኳሱ ጎን ለጎን ያሳደገንን ማህበረሰብ ለመድረስ ያላሰለሰ ጥረት እያደረግን ማህበረሰባዊ አላፊነታችንን እየተወጣን ነው ፡፡ ሆኖም ክለባችን እርዳታ ከሚያስፈልጋቸው እጻናት ጀምሮ እስከ አረጋዉያን ድረስ የበኩሉን የድጋፍ ሚና እየተወጣ ቢሆንም ከዚህ በተሻለ ለመስራት አዉንም የደጋፊዎቻችንን ድጋፍ ይሻል ፡፡
ተልዕኳችን ከሱስ የጸዳ በስፖርት የዳበረ እና ማህበራዊ አላፊነቱን የሚወጣ መልካም አርሃያ መሆን የሚችል ወጣት ማፍራት ነው ፡፡


ኢብራሂም ረሺድ የአዲስ ከቴ ዋና አሰልጣኝ


አሸናፊ ሲዳ የአዲስ ከቴ ፕረዝደንት


ምንተስኖት ሃብቴ የአዲስ ከቴ ፋይናንሻል ማናጀር


